ኢትዮጵያ 11,500 የጽንሰ ሐሳብ አቻ ስያሜዎችን ከብያኔዎቻቸው የያዘ አዲስ የሳይንስና ቴክኖሎጂ መዝገበ ቃላት አስመረቀች
11:17 11.11.2025 (የተሻሻለ: 11:24 11.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ 11,500 የጽንሰ ሐሳብ አቻ ስያሜዎችን ከብያኔዎቻቸው የያዘ አዲስ የሳይንስና ቴክኖሎጂ መዝገበ ቃላት አስመረቀች
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ የሳይንስ አካዳሚ አስተባባሪነት ከ30 በላይ የሙያ ዘርፎች ከ90 በላይ ዕውቅ ባለሙያዎች በዝግጅት እንደተሳተፉበት ታውቋል፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) “የሳይንስና ቴክኖሎጂ (እንግሊዘኛ-አማርኛ) መዝገበ ቃላት መጽሐፍ ሕትመት ተከናውኖ ለምረቃ መብቃቱ፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍን በመረዳት ወደ ተግባር ለመለወጥ ለሚደረገው ጥረት ትልቅ ፋይዳ አለው” ሲሉ በምረቃ ሥነ-ስርዓት ወቅት ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትሩ፣ በቀጣይ በብዙ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች እየተተረጎመ ተደራሽ እንዲሆን የማስቻል ሥራ ከኢትዮጵያ የሳይንስ አካዳሚ እና ሌሎች መሰል የምርምር ተቋማት ጋር መሠራት እንዳለበት በአፅንኦት ገልፀዋል፡፡
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መጽሐፉን ከማሳተም የመዝገበ ቃላቱን የሞባይል መተግበሪያ ማልማቱ መሥሪያ ቤቱ በማኅበራዊ ሚዲያው ላይ ያጋራው መረጃ ይጠቁማል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X