የምርጫ ታዛቢነት በፍጥነት እያደገ ባለው የሩሲያ እና ታንዛኒያ ግንኙነት ውስጥ አዲስ ዐምድ ሆኗል - ሩሲያዊ ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየምርጫ ታዛቢነት በፍጥነት እያደገ ባለው የሩሲያ እና ታንዛኒያ ግንኙነት ውስጥ አዲስ ዐምድ ሆኗል - ሩሲያዊ ባለሙያ
የምርጫ ታዛቢነት በፍጥነት እያደገ ባለው የሩሲያ እና ታንዛኒያ ግንኙነት ውስጥ አዲስ ዐምድ ሆኗል - ሩሲያዊ ባለሙያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 11.11.2025
ሰብስክራይብ

የምርጫ ታዛቢነት በፍጥነት እያደገ ባለው የሩሲያ እና ታንዛኒያ ግንኙነት ውስጥ አዲስ ዐምድ ሆኗል - ሩሲያዊ ባለሙያ

ጥቅምት 19 ቀን 2018 በታንዛኒያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ የሩሲያ የሲቪክ ቻምበር ልዑካን መገኘቱ ጠንካራ ምልክት ነው፤ ሲሉ በሞስኮ የከፍተኛ የንግድ ሥራ ትምህርት ቤት የአፍሪካ ጥናት ማዕከል ዳይሬክተር  አንድሬ ማስሎቭ ተናግረዋል።

"የልዑካኑ መገኘት በምርጫ ታዛቢነት ዘዴያችን ላይ የተቀመጠውን የመተማመን ደረጃ ያሳያል" በማለት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። አክለውም ይህ "በአሁኑ ጊዜ እያበበ በመጣው የሩሲያ-ታንዛኒያ ግንኙነት እድገት ውስጥ ትልቅ እርምጃ ነው" ብለዋል።

ባለሙያው በታንዛኒያ ያለውን የምርጫ ሂደት ብስለትም አድንቀዋል፡፡

"በአንድ በኩል፣ ባለሥልጣናት ለጽንፈኝነት ወይም ለጎዳና ላይ ሁከት ከመጠን በላይ ምላሽ አልሰጡም፤ በሌላ በኩል ደግሞ አጠቃላይ የምርጫው ሂደት ግልፅ ነው። አንድ ሚሊዮን ሰዎችን ያቀፈው ሲቪል ማኅበረሰብ፣ ሂደቱን በማደራጀት ተሳትፏል፤ ይህም ማንኛውንም ነገር ለመደበቅ በጣም አስቸጋሪ ያደርገዋል።"

ጥቅምት 19 በታንዛኒያ በታካሄደው የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በሥልጣን ላይ የሚገኙት ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሀሰን 97.66% ድምጽ በማግኘት ምርጫውን አሸንፈዋል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0