ጋዛ፣ ኤል-ዳባ እና የሩሲያ የኢንዱስትሪ ዞን በስዊስ - የኤል-ሲሲ እና ሾይጉ ስብሰባ ዋና ዋና ነጥቦች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱጋዛ፣ ኤል-ዳባ እና የሩሲያ የኢንዱስትሪ ዞን በስዊስ - የኤል-ሲሲ እና ሾይጉ ስብሰባ ዋና ዋና ነጥቦች
ጋዛ፣ ኤል-ዳባ እና የሩሲያ የኢንዱስትሪ ዞን በስዊስ - የኤል-ሲሲ እና ሾይጉ ስብሰባ ዋና ዋና ነጥቦች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 10.11.2025
ሰብስክራይብ

ጋዛ፣ ኤል-ዳባ እና የሩሲያ የኢንዱስትሪ ዞን በስዊስ - የኤል-ሲሲ እና ሾይጉ ስብሰባ ዋና ዋና ነጥቦች

የሩሲያ የደህንነት ምክር ቤት ፀሐፊ በዛሬው ዕለት ካይሮ ውስጥ ከፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ ኤል-ሲሲ ጋር ውይይት ማድረጋቸውን የፕሬዝዳንት አስተዳደር አስታውቋል።

የውይይቱ ቁልፍ ሐሳቦች ፦

🟠 የግብፅ ፕሬዝዳንት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የጠበቀ፣ ቋሚ እና ተለዋዋጭ ግንኙነት ግብፅ እንደምታደንቅ በመግለጽ ለፕሬዝዳንት ቭላዲሚር ፑቲን ሰላምታ አስተላልፈዋል።

🟠 ሰርጌይ ሾይጉ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ለግብጹ አቻቸው ሰላምታ ማስተላለፋቸውን ገልጸው፣ ሩሲያ የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን የበለጠ ለማዳበር እና ለማጠናከር ያላትን ፍላጎት አጽንኦት ሰጥተዋል።

🟠 ኤል-ሲሲ በመካከለኛው ምስራቅ መረጋጋትን፣ አንድነትን እና ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ጥረቶችን መቀጠል አስፈላጊ መሆኑን አስምረውበታል።

🟠ሁለቱም ወገኖች በግብፅና በሩሲያ መካከል የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን ለማጠናከር የሚቻልባቸውን መንገዶች እንዲሁም  ፖለቲካ፣ ንግድና የኢንቨስትመንት ጨምሮ በሌሎች ዘርፎች ዙሪያ ያሉትን የልማት ተስፋዎች ተወያይተዋል።

🟠 ተሳታፊዎቹ በስዊስ ካናል ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ውስጥ የሩሲያ የኢንዱስትሪ ዞን ለመመስረት ከኤል-ዳባ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ጎን ለጎን የተያዙትን እቅዶች ተወያይተዋል።

🟠 በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት የሁለት መንግሥታት መፍትሄን ተግባራዊ ማድረግ እና የፍልስጤም መንግሥት መመሥረት በቀጣናው ፍትሐዊ እና ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ብቸኛው መንገድ ነው ሲሉ ኤል-ሲሲ አስታውቀዋል።

🟠 ፕሬዝዳንት አል-ሲሲ የዩክሬይንን ቀውስ ለመፍታት እና ዓለም አቀፍ ሰላም ለማስፈን የሚደረጉትን ሁሉንም ጥረቶች ሀገራቸው እንደምትደግፍ በድጋሚ አረጋግጠዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0