ሩሲያ በአፍሪካ በሰው ሠራሽ አስተውሎት ዘርፍ የሚደረጉ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን ለማገዝ የሚያስችል የድጋፍ መርሃ ግብር ይፋ አደረገች
19:37 10.11.2025 (የተሻሻለ: 19:54 10.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሩሲያ በአፍሪካ በሰው ሠራሽ አስተውሎት ዘርፍ የሚደረጉ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን ለማገዝ የሚያስችል የድጋፍ መርሃ ግብር ይፋ አደረገች
መርሃ ግብሩ የሩሲያ - አፍሪካ ትረስትድ ኤ.አይ. ጉባኤ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አስተናጋጅነት መካሄድ በጀመረበት በዛሬው ዕለት ይፋ ሆኗል።
በጉባኤው ንግግር ያደረጉት የሞስኮው የኮሙኒኬሽን እና የኢንፎርማቲክስ ቴክኒካል ዩኒቨርስቲ ሬክተር ሰርጌይ ኤሮኪን (ፕ/ር ) መርሃ ግብሩ የሩሲያ እና አፍሪካን የረዥም ጊዜ አጋርነት የበለጠ እንደሚያጠናክር ገልጸዋል፡፡
ሰርጌይ፣ በሚቀጥለው ዓመት እስከ 100,000 ዶላር የገንዘብ ድጋፍ የሚያስገኝ ውድድር እንደሚካሄድም አስታውቀዋል፡፡
"አፍሪካ ሰው ሠራሽ አስተውሎት ከመሳሰሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች የተጣጣመ እድገትን ለማስመዝገብ የሚያስችል ያልተነካ እምቅ አቅም አላት" ብለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ በበኩላቸው፣ ጉባኤው በሩሲያና አፍሪካ የኤ.አይ. ባለሙያዎች መካከል የሚደረገውን ዓለምአቀፍ ውይይት እንደሚያሳድግ ገልጸው "እውቀት ድንበር ዘለል ሲሆን ለውጥ ያመጣል" ብለዋል።
ጉባኤው ዛሬን ጨምሮ ለቀጣዮቹ ሦስት ቀናት የሚቀጥል ይሆናል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

