አውሮፓውያን አገራት ለአሜሪካ ወታደሮች ክፍያ ለመፈፀም መገደዳቸው ተዘገበ
14:36 10.11.2025 (የተሻሻለ: 14:44 10.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
አውሮፓውያን አገራት ለአሜሪካ ወታደሮች ክፍያ ለመፈፀም መገደዳቸው ተዘገበ
አንዳንድ የአውሮፓ አገራት በአሜሪካ መንግሥት መዘጋት ምክንያት የአሜሪካ የጦር ሰፈሮችን ወጪ በራሳቸው ለመሸፈን መገደዳቸውን የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
ከተጀመረ ስድስት ሳምንት ሊሞላው ጥቃት ቀናት በቀረው የአሜሪካ መንግሥት መዘጋት ጊዜ ውስጥ በአውሮፓ በሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች (ወታደራዊ ጣቢያዎች) የሚሠሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ያለክፍያ ቆይተዋል።
አንዳንድ የአሜሪካ ጦር ሰፈር አስተናጋጅ አገራት መንግሥታት አሜሪካ መልሳ ትከፍለናለች በሚል ተስፋ ወጪዎቹን ሸፍነዋል። ጣሊያንን እና ፖርቹጋልን ጨምሮ በሌሎች አገራት ደግሞ ሠራተኞች ያለክፍያ መሥራታቸውን ቀጥለዋል።
"ይህ ምክንያታዊ ያልሆነ ሁኔታ ነው ምክንያቱም ማንም መልስ የለውም፤ ማንም ኃላፊነት የሚሰማው የለም። ይህ በእኛ በጣሊያናውያን ሠራተኞች ላይ አስደንጋጭ ውጤት እያመጣ ነው" ሲሉ በሰሜን ምስራቅ ጣሊያን በሚገኘው አቪያኖ አየር ማረፊያ የሠራተኞች ማኅበር አስተባባሪ የሆኑት አንጄሎ ዛካሪያ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X