ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በታሪክ ተመራማሪው ላጲሶ ጌ. ዴሌቦ ሕልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ገለፁ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በታሪክ ተመራማሪው ላጲሶ ጌ
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በታሪክ ተመራማሪው ላጲሶ ጌ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 10.11.2025
ሰብስክራይብ

ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በታሪክ ተመራማሪው ላጲሶ ጌ. ዴሌቦ ሕልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ገለፁ

"ላጲሶ (ፕ/ር) በኢትዮጵያ የሥነ-መንግሥት ታሪክ ምርምርና የላቀ የዕውቀት ሥርፀት ላደረጉት አስተዋፅኦ ሲታወሱ ይኖራሉ" ሲሉ ፕሬዝዳንቱ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው የሐዘን መግለጫ አስተላልፈዋል።

ፕሬዝዳንቱ ለቤተሰቦቻቸው እና ወዳጅ ዘመዶቻቸውም መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በበኩላቸው "አንጋፋው የታሪክ ምሁር ፕሮፌሰር ላዺሶ ጌ. ዴሌቦ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ማለፋቸውን በታላቅ ኀዘን ሰማሁ" ሲሉ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ሐዘናቸውን አጋርተዋል።

በትናንትናው ዕለት በ87 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ፕሮፌሰር ላዺሶ ጌ. ዴሌቦ የአስክሬን ሽኝትና የቀብር ሥነ ስርዓት ማክሰኛ ሕዳር ዐ2 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚፈፀም የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0