የአሜሪካ ሴኔት የ40 ቀናት የአሜሪካ መንግሥት መዘጋትን ለመቋጨት መንገድ ከፋች ስምምነት አፀደቀ
የአሜሪካ ሴኔት የ40 ቀናት የአሜሪካ መንግሥት መዘጋትን ለመቋጨት መንገድ ከፋች ስምምነት አፀደቀ
የአሜሪካ ሴኔት *ፊሊበስተርን ለማለፍ የሚያስፈልገውን የ60 ድምጽ ገደብ ከደረሰ በኋላ የ40 ቀናት የመንግሥት መዘጋት እንዲያበቃ ድምጽ ሰጥቷል።
የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት፣ ሴናተር ጆን ኮርኒን ወሳኙን ድምጽ በመስጠት፣ የሁለት ፓርቲዎችን ያሳተፈ ቀጣይነት ያለው ውሳኔ ጊዜያዊ ይሁንታን አግኝተዋል።
ይህ እርምጃ እስከ ጥር 22 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለመንግሥት ሥራዎች የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋል፡፡ በቅርብ ጊዜ በተደረጉ ቅነሳዎች የተጎዱ የፌዴራል ሠራተኞችን ወደ ሥራ ገበታቸው ይመልሳል፤ የተጨማሪ የምግብ እርዳታ ፕሮግራም (SNAP) የምግብ እርዳታን እስከ 2026 የበጀት ዓመት ድረስ ያድሳል።
ስምንት ዲሞክራቶች ከሪፐብሊካኖች ጋር በመቀላቀል፣ ድምጹ ለረቂቅ ሕጉ የመጨረሻ ማለፍ እና ለተከታዩ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይሁንታ መንገድ ከፍቷል፤ ይህም የፌዴራል አገልግሎቶች እንደገና እንዲከፈቱና የሳምንታት መስተጓጎል እንዲያበቃ ያደርጋል።
* ፊሊበስተር አንድ ወይም ከዚያ በላይ የሕግ አውጪ አባላት ውሳኔን ለማዘግየት ወይም ሙሉ በሙሉ ለመከላከል ሲሉ በቀረበው ረቂቅ ሕግ ላይ ክርክርን የሚያራዝሙበት የፓርላማ አሠራር ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X