49 ተቋማት የሚሳተፉበት የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የስፖርት ፌስቲቫል በጅማ ከተማ ሊካሄድ ነው
15:45 09.11.2025 (የተሻሻለ: 15:54 09.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
49 ተቋማት የሚሳተፉበት የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የስፖርት ፌስቲቫል በጅማ ከተማ ሊካሄድ ነው
የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ስፖርት ማኅበር እንዳስታወቀው፣ ቀደም ብሎ በአምስት ክላስተሮች ውድድር ለማካሄድ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም አዘጋጅ ተቋማት ዝግጁ ባለመሆናቸው አገር አቀፍ ፌስቲቫል ለማከናወን ተወስኗል፡፡
ፌስቲቫሉ በ15 የስፖርት አይነቶች ከጥር 9-24 ድረስ የሚካሄድ ሲሆን ለውድድሩ በቂ ዝግጅት መደረጉ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ አስታውቋል፡፡
በተለያዩ ምክንያቶች ለ8 ዓመታት ያህል ተቋርጦ የነበረው ይህ ውድድር፤ ባለፈው ዓመት በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት በአምስት የስፖርት አይነቶች መጀመሩ ይታወሳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X