ሞስኮ እና ካይሮ በሱዳን ግጭት እልባት ዙሪያ መከሩ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሞስኮ እና ካይሮ በሱዳን ግጭት እልባት ዙሪያ መከሩ
ሞስኮ እና ካይሮ በሱዳን ግጭት እልባት ዙሪያ መከሩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 09.11.2025
ሰብስክራይብ

ሞስኮ እና ካይሮ በሱዳን ግጭት እልባት ዙሪያ መከሩ

የሩሲያ እና የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ባደረጉት የስልክ ውይይት በሱዳን ያለውን ሁኔታ ጨምሮ ሰፋ ባሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

ከግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከተው ሚኒስትሮቹ፡-

🟠 የሱዳንን መንግሥት፣ ተቋማቱን እና አንድነቱን ማስጠበቅ እንደሚያስፈልግ በድጋሚ አረጋግጠዋል፤ እንዲሁም ማንኛውንም የትይዩ ተቋም ምሥረታም እንደማይቀበሉ ገልጸዋል።

🟠 በአሁኑ ወቅት በፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች አማፂያን ቁጥጥር ስር የምትገኘው አል-ፋሸር በአስቸኳይ ሰብአዊ እርዳታ እንደሚያስፈልጋት አጽንኦት ሰጥተዋል።

🟠 ስለተዘገቡት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ስጋታቸውን ገልጸዋል።

🟠 ግጭቱን ለመፍታት በ"ሱዳን አራትዮሽ" (ግብፅ፣ አሜሪካ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች እና ሳዑዲ አረቢያ) ማዕቀፍ ውስጥ ትብብር ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አስምረውበታል።

ከሱዳን ባሻገር፣ ሚኒስትሮቹ የአል-ዳባ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት እና ከስዊዝ ካናል አቅራቢያ የሚገኘውን የሩሲያ የኢንዱስትሪ ዞን በተመለከተም ተወያይተዋል።

እነዚህ ተነሳሽነቶች "በግብፅ የሩሲያን ኢንቨስትመንት ለመጨመር እና በሁለቱ አገራትይ መካከል ያለውን ትብብር ለማጠናከር አስተዋፅኦ ያደርጋሉ" ብለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0