ኔቶ ለዩክሬን ሲል ሦስተኛውን የዓለም ጦርነት እንደማይጀምር ስቶልተንበርግ ማመናቸውን ተዘገበ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኔቶ ለዩክሬን ሲል ሦስተኛውን የዓለም ጦርነት እንደማይጀምር ስቶልተንበርግ ማመናቸውን ተዘገበ
ኔቶ ለዩክሬን ሲል ሦስተኛውን የዓለም ጦርነት እንደማይጀምር ስቶልተንበርግ ማመናቸውን ተዘገበ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 09.11.2025
ሰብስክራይብ

ኔቶ ለዩክሬን ሲል ሦስተኛውን የዓለም ጦርነት እንደማይጀምር ስቶልተንበርግ ማመናቸውን ተዘገበ

የኔቶ የቀድሞ ዋና ጸሐፊ ጄንስ ስቶልተንበርግ ለምዕራብ ሚዲያ እንደተናገሩት፣ እ.ኤ.አ. በየካቲት 2022 ቮሎዲሚር ዘለንስኪ በዩክሬን ላይ “በረራ የተከለከለ ቀጣና” እንዲቋቋም ያቀረቡትን ጥያቄ ውድቅ አድርገዋል፡፡ ምክንያቱም ይህ የሩሲያ እና የቤላሩስ የአየር መከላከያዎችን መምታት ማለት ሲሆን፣ ይህም ከኔቶ ጋር ቀጥተኛ ጦርነትን የሚያስጀምር እርምጃ ነው።

  “በአየር ላይ የሩሲያ አውሮፕላን ወይም ሄሊኮፕተር ካለ፣ እኛ እሱን መተን መጣል አለብን፤ ያኔ በኔቶ እና በሩሲያ መካከል ሙሉ ጦርነት ይሆናል። እናም እኛ ያንን ለማድረግ ፈቃደኛ አይደለንም” ሲሉ  ስቶልተንበርግ ተናግረዋል። አክለውም የባይደን ውሳኔም ተመሳሳይ እንደነበር ገልጸዋል፡- “ለዩክሬን ሲባል የሦስተኛውን የዓለም ጦርነት አደጋን አንወስድም”።



በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0