የአፍሪካ ኅብረት በናይጄሪያ ጉዳይ
21:12 08.11.2025 (የተሻሻለ: 21:14 08.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ኅብረት በናይጄሪያ ጉዳይ
ከአሜሪካ የኃይል አካሄድ ለዲፕሎማሲ ቅድሚያ እንዲሰጥ አሳሰበ
የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን አሜሪካ በቅርቡ የናይጄሪያ መንግሥት ክርስቲያኖችን ያሳድዳል በሚል ከሳ፤ ስለ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ማንሳቷ እንዳሳሰበው ገልጿል።
ኅብረቱ በመግለጫው፤ ከአንድ ወገን ማስፈራሪያ ይልቅ ለዲፕሎማሲያዊ ውይይት፣ የመረጃ ልውውጥ እና የአቅም ግንባታ አጋርነቶች ጥሪ አቅርቧል።
ኅብረቱ በተጨማሪም፦
🟠 የናይጄሪያን ሉዓላዊነት ሙሉ በሙሉ እንደሚደግፍ፣
🟠 ለናይጄሪያ መረጋጋት እውቀት፣ የሥልጠና ፕሮግራሞች እና የክልላዊ አሠራሮችን ለማቀናጀት ዝግጁነቱን፤
🟠 ለክልላዊ መረጋጋት፣ ትስስር እና የፀረ-ሽብር ተልዕኮዎች የናይጄሪያን አስተዋጽኦ እውቅና እንደሚሰጥ በመግለጫው አስምሮበታል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X