በሞስኮ የሱዳን ኤምባሲ ለኤል-ፋሸር ሰለባዎች በተካሄደ መታሰቢያ፤ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች አማጺያኑን በመደገፍ ተከሰሰች

ሰብስክራይብ

በሞስኮ የሱዳን ኤምባሲ ለኤል-ፋሸር ሰለባዎች በተካሄደ መታሰቢያ፤ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች አማጺያኑን በመደገፍ ተከሰሰች

በድጋፍ ሰልፉ የተሰባሰቡ በሩሲያ በሚኖሩ ሱዳናውያን ዳያስፖራዎች እና የሱዳን ተማሪዎች ማህበር፤ በሰሜን ዳርፉር የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ኤል ፋሸርን በመቆጣጠራቸው ለተጎዱ ሰለባዎች የመታሰቢያ ዝግጅት አካሂደዋል።

በሞስኮ የዲፕሎማሲ ሚሲዮኖች ተወካዮች በተገኙበት ዝግጅት፤ የሱዳን አምባሳደር መሀመድ ሲራጅ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን ድርጊት አውግዘው ዓለም አቀፍ ተጠያቂነት እንዲኖር ጠይቀዋል።

"የዛሬው ዝግጅት ዓላማ በኤል-ፋሸር በዓማፂ ሚሊሻዎች የተፈጸሙትን አሰቃቂ ወንጀሎች ማጋለጥ ነው። በየቀኑ ሲቪሎችን ያጠቃሉ፣ በዘፈቀደ ይገድላሉ እንዲሁም ሰዎችን ያሰቃያሉ" ሲሉ አምባሳደሩ ባደረጉት ንግግር ገልፀዋል ።

ወንጀሎቹ የተፈፀሙት አማጺያኑ ከተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በሚያገኙት የፖለቲካ እና ወታደራዊ ድጋፍ ነው ሲሉ አስረግጠዋል።

"የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በአሸባሪ ድርጅትነት እንዲሰይም እና አመራሮቹን እና የወንጀሎቹን ተባባሪዎች ሁሉ ተጠያቂ እንዲያደርግ ጥሪ እናቀርባለን" ብለዋል።

የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን በመደገፍ የቀረበባትን ክስ ውድቅ አድርጋለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
በሞስኮ የሱዳን ኤምባሲ ለኤል-ፋሸር ሰለባዎች በተካሄደ መታሰቢያ፤ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች አማጺያኑን በመደገፍ ተከሰሰች - Sputnik አፍሪካ
1/3
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
በሞስኮ የሱዳን ኤምባሲ ለኤል-ፋሸር ሰለባዎች በተካሄደ መታሰቢያ፤ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች አማጺያኑን በመደገፍ ተከሰሰች - Sputnik አፍሪካ
2/3
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
በሞስኮ የሱዳን ኤምባሲ ለኤል-ፋሸር ሰለባዎች በተካሄደ መታሰቢያ፤ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች አማጺያኑን በመደገፍ ተከሰሰች - Sputnik አፍሪካ
3/3
1/3
2/3
3/3
አዳዲስ ዜናዎች
0