በኢትዮጵያ የጥቅምት ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት መጠን ቅናሽ አሳየ
18:40 08.11.2025 (የተሻሻለ: 18:44 08.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በኢትዮጵያ የጥቅምት ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት መጠን ቅናሽ አሳየ
11.7 በመቶ ሆኖ የተመዘገበው ግሽበት መጠኑ በመስከረም ወር ከነበረበት 13.2 በመቶ ዝቅ ማለቱን የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት መረጃ አመላክቷል።
ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ከተመዘገበው 19.3 በመቶ የዋጋ ግሽበት ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ቅናሽ የታየበት ሆኗል።
በሪፖርቱ መሠረት፦
በወሩ የምግብ ነክ ዕቃዎች 10.2 በመቶ እንዲሁም ምግብ ነክ ያልሆኑ እቃዎች ደግሞ 14.2 በመቶ ሆነው ተመዝግበዋል።
የምግብ ነክ ያልሆኑ ዕቃዎች የዋጋ ግሽበት መጠን ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 14.2 በመቶ ከፍ ብሏል።
የታየው ቅናሽ የተሻሻለ የአቅርቦት ሁኔታዎችን እና በመመሪያ የተደገፈ የገበያ መረጋጋትን ይጠቁማል መባሉን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X