ዛምቢያ ለረጅም ጊዜ የሚሠራ የኤችአይቪ መከላከያ መርፌን ያስመዘገበች ሁለተኛዋ የአፍሪካ ሀገር ሆነች
18:00 08.11.2025 (የተሻሻለ: 18:04 08.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ዛምቢያ ለረጅም ጊዜ የሚሠራ የኤችአይቪ መከላከያ መርፌን ያስመዘገበች ሁለተኛዋ የአፍሪካ ሀገር ሆነች
የጤና ሚኒስትር ኤላይጃ ሙቺማ፤ አዲስ የተመዘገበው ሌናካፓቪር የተሰኘው መርፌ በየስድስት ወሩ አንድ ጊዜ የሚሰጥ ሲሆን በዚህ ጊዜ ከኤችአይቪ የመከላከል አቅምን ይሰጣል ሲሉ በሉሳካ በተካሄደ ይፋዊ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተናግረዋል።
ሌናካፓቪር መፍትሄ የሚሆንላቸው፦
🟠 ለነፍሰ ጡር እና የሚያጠቡ ሴቶች፣
🟠 ዕለታዊ ወይም በየሁለት ወሩ የሚሰጡ የኤችአይቪ መከላከያ መርሃ-ግብሮችን መከተል ለማይችሉ ሰዎች፣
🟠 መከላከያ እርምጃዎችን በሚስጢር ማግኘት ለሚፈልጉ ወንዶች።
ህክምናው ብቁ ለሆኑ ሁሉም ዜጎች በነፃ እንደሚሰጥ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።
በፕሬዝዳንት ሃካይንዴ ሂቺሌማ አመራር ስር ዛምቢያ በኤችአይቪ ላይ በሚደረገው ትግል ዓለም አቀፍ መሪ ሆና እንደምትቀጥል አጽንኦት ሰጥተዋል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X