ከክሪፕቶ ማይኒንግ ባለፉት ሶስት ወራት 82.9 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱ ተገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱከክሪፕቶ ማይኒንግ ባለፉት ሶስት ወራት 82
ከክሪፕቶ ማይኒንግ ባለፉት ሶስት ወራት 82 - Sputnik አፍሪካ, 1920, 08.11.2025
ሰብስክራይብ

ከክሪፕቶ ማይኒንግ ባለፉት ሶስት ወራት  82.9 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱ ተገለፀ

በሩብ ዓመቱ የተመዘገበው ይህ የገቢ መጠን የኢንቨስትመንት ፍቃድ አግኝተው ለሚንቀሳቀሱ 25 ኩባንያዎች ከቀረበ ኃይል የተገኘ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ሞገስ መኮንን ተናግረዋል።

በ2017 ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተገኘው 27.9 ሚሊዮን ዶላር ጋር ሲነፃፀር የሶስት እጥፍ ጭማሪ ማሳየቱንም ጠቁመዋል። በበጀቱ ዓመቱ ከዘርፉ ለማግኘት ታቅዶ የነበረው 73.1 ሚሊዮን ዶላር ነበር።

"ክሪፕቶ ማይኒንግ ከሚጠይቀው ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል አንፃር የታዳሽ ኃይል ከፍተኛ አቅርቦት ያላት ኢትዮጵያ ተመራጭ መሆን ችላለች" ሲሉም ኃላፊው ጨምረው ገልፀዋል።

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0