አሜሪካ ደቡብ አፍሪካ በሚካሄደው የቡድን 20 ስብሰባ እንደማትካፈል ትራምፕ በይፋ አስታወቁ
14:54 08.11.2025 (የተሻሻለ: 15:04 08.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
አሜሪካ ደቡብ አፍሪካ በሚካሄደው የቡድን 20 ስብሰባ እንደማትካፈል ትራምፕ በይፋ አስታወቁ
ዶናልድ ትራምፕ የደቡብ አፍሪካ ባለሥልጣናት የሀገሪቱን ነጭ ዜጎች መብት ይጥሳሉ በማለት ያቀረቡት ክስ ለውሳኔያቸው መነሻ እንደሆነ ገልፀዋል።
“ቡድን 20 በደቡብ አፍሪካ መካሄዱ እጅግ አሳፋሪ ነው” ሲሉ ፕሬዝዳንቱ በትሩዝ ሶሻል ማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ጽፈዋል።
“የደች፣ የፈረንሳይ እና የጀርመን ዝርያ ያላቸው 'አፍሪካነር' ሰፋሪዎች እየተገደሉና እየታረዱ እንዲሁም መሬታቸውና እርሻዎቻቸው በሕገ-ወጥ መንገድ እየተወረሱ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።
ትራምፕ በስብሰባው ላይ እንደማይገኙ ጥቅምት 26 አስቀድመው ገልጸው ነበር።
የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የነጭ ዜጎች የዘር ማጥፋት ክሱን የሚከላከል መግለጫ በምላሹ አውጥቷል። ሀገሪቱ አሜሪካ የአፍሪካነር ዝርያ ያላቸው የነጭ ደቡብ አፍሪካውያን የስደተኝነት ጥያቄዎችን ቅድሚያ ለመስጠት መወሰኗን ከዚህ በፊት ተችታለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X