ኢትዮጵያና ሳዑዲ በዲጂታል እና ኢ-አገልግሎቶች ዘርፍ ትብብር ለማጠናከር ተስማሙ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያና ሳዑዲ በዲጂታል እና ኢ-አገልግሎቶች ዘርፍ ትብብር ለማጠናከር ተስማሙ
ኢትዮጵያና ሳዑዲ በዲጂታል እና ኢ-አገልግሎቶች ዘርፍ ትብብር ለማጠናከር ተስማሙ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 08.11.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያና ሳዑዲ በዲጂታል እና ኢ-አገልግሎቶች ዘርፍ ትብብር ለማጠናከር ተስማሙ

የኢትዮጵያ ሥራ ፈጣሪ ወጣቶች ማኅበር እና ሙንሻአት አገልግሎት በጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ዘርፍ አብረው ለመሥራት የሚያስችል ስትራቴጂያዊ ትብብር ፈጥረዋል፡፡

አጋርነቱ በኢትዮጵያውያን ሥራ ፈጣሪዎች እና የሳዑዲ አቻዎቻቸው መካከል የእውቀት እና የቴክኖሎጂ ልውውጥን በማበረታታት፣ መስራቾችን እና ጀማሪ ኩባንያዎችን ለማገናኘት ያግዛል ተብሏል።

"የአቅም ግንባታ እና ድንበር ተሻጋሪ የገበያ ተደራሽነትን ይበልጥ ለማስፋት እድል የሚፈጥር ነው" ሲሉ በሳዑዲ ዓረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር ከድር በሪያድ እየተካሄደ ካለው የቢባን 2025 ፎረም ጎን ለጎን በተፈረመው ስምምነት ላይ ተናግረዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0