ኮንጎ እና ሩዋንዳ የሰላም ሂደቱን ያራምዳል የተባለ የመጀመሪያ የኢኮኖሚ ስምምነት በዋሽንግተን ተፈራረሙ
12:29 08.11.2025 (የተሻሻለ: 12:34 08.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኮንጎ እና ሩዋንዳ የሰላም ሂደቱን ያራምዳል የተባለ የመጀመሪያ የኢኮኖሚ ስምምነት በዋሽንግተን ተፈራረሙ
“የክልላዊ ኢኮኖሚ ውህደት ማዕቀፍ በሁለቱ ሀገራት መካከል የኢኮኖሚ ትብብር እና ልማትን ለማበረታታት ቁልፍ መስኮችን ይዘረዝራል” ሲል የኮንጎ-ሩዋንዳ የክትትል ኮሚቴ የጋራ ስብሰባን ተከትሎ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
በትራምፕ አደራዳሪነት የተፈረመው የስምምነቱ የመጨረሻ ፊርማ የሀገራቱ መሪዎች በተገኙበት በኋይት ሀውስ እንደሚከናወን ይጠበቃል። ሆኖም ይፋዊ የስምምነቱ ቀን አልተገለፀም።
የዚህ የኢኮኖሚ ማዕቀፍ ትግበራ የሩዋንዳ ወታደሮች ከምስራቃዊ ኮንጎ መውጣትን እና ኮንጎ መቀመጫውን ባደረገው የሩዋንዳ ነፃ አውጪ ደሞክራሲያዊ ኃይል ታጣቂ ቡድን ላይ የሚደረጉ ዘመቻዎችን ጨምሮ በቀድሞ የጸጥታ ግዴታዎች አጥጋቢ አፈፃፀም ላይ የተመሠረተ ነው።
መግለጫው እንዳመለከተው፤ የጋራ የክትትል ኮሚቴው በእነዚህ የጸጥታ እርምጃዎች ዙሪያ "ሂደቱ እንደዘገየ" ተቀብሎ ትግበራዉን ለማጠናከር ቃል ገብቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X