ኢትዮጵያ 32ኛውን የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ለማስተናገድ ይፋዊ ጥያቄ አቀረበች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ 32ኛውን የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ለማስተናገድ ይፋዊ ጥያቄ አቀረበች
ኢትዮጵያ 32ኛውን የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ለማስተናገድ ይፋዊ ጥያቄ አቀረበች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 08.11.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ 32ኛውን የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ለማስተናገድ ይፋዊ ጥያቄ አቀረበች

ሀገሪቱ ጉባዔውን ለማስተናገድ ልምዱም አቅሙም እንዳላት የገለፁት በብራዚል የኢትዮጵያ አምባሳደር ልዑልሰገድ ታደሰ፤ ሀገራት ድጋፍ እንዲሰጡ ጠይቀዋል፡፡

የአረንጓዴ ዐሻራ፣ የማይበገር የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የሚያግዙ ተግባራዊ ሥራዎችን ያከናወነችው ኢትዮጵያ፤ ጉባኤውን ለማስተናገድ ፍላጎቱም ዝግጁነቱም አላት ብለዋል፡፡

አምባሳደር ልዑልሰገድ ለማሳያነትም፦

ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎችን በማዘጋጀት የረጅም ጊዜ ልምድ እንዳካበትች፣

የላቀ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት እንዳላት፣

ከ160 በላይ ለሆኑ የዲፕሎማሲ ተቋማት ጽህፈት ቤቶች መቀመጫ እንደሆነች አንስተዋል፡፡

አምባሳደሩ ጥያቄውን ያቀረቡት በብራዚል እየተካሄደ በሚገኘው 30ኛው የዓለም የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ ነው፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0