ኢትዮጵያ ከካካዎ ምርት ተጠቃሚ መሆን እንድትችል የባለድርሻ አካላት ትብብር እና ጥረት ወሳኝ ነው - የካካዎ ተመራማምሪ
11:16 08.11.2025 (የተሻሻለ: 11:24 08.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ከካካዎ ምርት ተጠቃሚ መሆን እንድትችል የባለድርሻ አካላት ትብብር እና ጥረት ወሳኝ ነው - የካካዎ ተመራማምሪ
ሀገሪቱ ሰብሉን ለማምረት ምቹ ሥነ-ምህዳር አላት የሚሉት አቡኪያ ጌቱ፤ ከግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር የኢትዮጵያን የካካዎ ፍሬ በመጠቀም የተሠራው ለሀገሪቱ የመጀመሪያው ቸኮሌት፤ በዓለም ላይ አሁን ከሚገኙ ቸኮሌቶች ተወዳዳሪ እንደሆነ ማረጋገጥ መቻሉን ለስፑትኒክ አፍሪካ በሰጡት ቃል ገልጸዋል።
“ኢትዮጵያ ውስጥ ካካዎ መመረት ይችላል። ለዚህም የሚሆን ደግሞ ለብዙ ዓመታት የተለፋበት፤ ምርምር የተደረገበት ዝርያ የማስመዝገብ ሥራ እንደ ሀገር ተሠርቷል። በአሁኑ ሰዓት ካካዎን ከስልሳ ሄክታር በላይ መሬት ላይ ተክለናል። በቀጣይ ደግሞ በመቶ ሺህ ሄክታሮች የሚሰፋበት ሁኔታ ነው የሚኖረው። ይህን ለማድረግ ግን የመንግሥት፤ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን የጋራ ጥረት ይጠይቃል” ብለዋል፡፡
ተመራማሪው ዘርፉ ተገቢውን ትኩረት የሚያገኝ ከሆነ ኢትዮጵያ በአጭር ግዜ ውስጥ የካካዎ ምርት ላኪ መሆን እንደምትችል ጠቁመዋል፡፡
“ኤክስፖርት ስናደርግ ደግሞ እንደሌሎቹ ሀገራት ጥሬ እቃውን ብቻ ሳይሆን እሴት ጨምረን መላክ አለብን፡፡ የተለያዩ ምርቶችን ኤክስፖርት ካደረግን በዓለም የምንታወቅ ሀገር እንሆናለን፡፡”
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X