አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የኒውክሌር ሬአክተር የልህቀት ማዕከል ለማቋቋም ማቀዱ ተነገረ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የኒውክሌር ሬአክተር የልህቀት ማዕከል ለማቋቋም ማቀዱ ተነገረ
አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የኒውክሌር ሬአክተር የልህቀት ማዕከል ለማቋቋም ማቀዱ ተነገረ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 08.11.2025
ሰብስክራይብ

አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የኒውክሌር ሬአክተር የልህቀት ማዕከል ለማቋቋም ማቀዱ ተነገረ

ማዕከሉን ከኢትዮጵያ የ10 ዓመት የልማት እቅድ ጋር በማጣመር በአህጉሪቱ በኒውክሌር ቴክኖሎጂ መሪ ለመሆን ውጥን መያዙን የዩኒቨርሲቲው የምርምርና የልህቀት ማዕከል ዳይሬክተር ጌታቸው አዳም (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

በዘርፉ ብቁ ባለሙያዎችን ለማግኘት ዩኒቨርሲቲው የሰው ሀብት አቅሙን በላቁ የሥልጠና ፕሮግራሞች እና በዓለም አቀፍ ትብብር እያሳደገ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡

ዕቅዱ ኒውክሌር ሳይንስን ለሰላማዊ እና ለልማታዊ ዓላማዎች ማዋልን ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ከቀጣናው ሀገራት ዜጎች ባሻገር ያሉ ሀገራትንም በሥልጠናው ተደራሽ የማድረግ ራዕይ መሰነቁን ኃላፊው ገልጸዋል።

◻ ከዓለም አቀፍ የኒውክሌር ኃይል ኤጀንሲ፣ አዲስ ከተመሠረተው የኒውክሌር ኃይል ኮሚሽን እና ከሌሎች ተቋማት ጋር ትብብርን ማጠናከር ዘርፉ ዓለም አቀፍ ፕሮቶኮሎችን ተከትሎ እንዲመራ እንደሚያደርገው ገልጸዋል።

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0