የሶማሊያ የባሕር ላይ ወንበዴዎች ከ2024 ወዲህ እጅግ ከባድ የተባለውን ጥቃት ፈፀሙ

የሶማሊያ የባሕር ላይ ወንበዴዎች ከ2024 ወዲህ እጅግ ከባድ የተባለውን ጥቃት ፈፀሙ
ወንበዴዎቹ በማልታ ባንዲራ ስር ቤንዚን ጭኖ ይጓዝ የነበረ የነዳጅ መርከብን ከሶማሊያ የባሕር ዳርቻ አጠገብ በኃይል መውረራቸው ተገልጿል። በመርከቧ ውስጥ የነበሩ 24 ሠራተኞች በደህንነት ክፍል ውስጥ በመደበቅ ሁኔታውን ተቆጣጥረው እንደቆዩ የተለያዩ ምንጮች ዘግበዋል።
ሄላስ አፍሮዳይት የተባለችው እና በግሪኩ ላስኮ ማሪን ማኔጅመንት ኩባንያ የምትተዳደረው መርከቧ፤ ከህንድ ሲካ ወደ ደቡብ አፍሪካ ደርባን በመጓዝ ላይ ነበረች።
ጥቃት ፈፃሚዎቹ መርከቧ ላይ ከመውጣታቸው በፊት በቁጥጥራቸው ሥር ከነበረች አነስተኛ የኢራን የሸራ መርከብ ባንቀሳቀሱት ፈጣን ጀልባ በአውቶማቲክ መሳሪያዎች እና በሮኬት ማስወንጨፊያ ተኩስ እንደከፈቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
ክስተቱ የተፈፀመው ከሶማሊያዋ ሆብዮ በግምት 550 የባሕር ማይል ርቀት ላይ እና በተለምዶ ከፍተኛ ስጋት ካለባቸው አካባቢዎች እጅግ በራቀ ቦታ ነው። በመርከቧ ላይ የታጠቁ ጠባቂዎች አልነበሩም ተብሏል።
ዓለም አቀፍ ምላሽ፦
በምላሹም በአፍሪካ ቀንድ የባሕር ውንብድናን የሚዋጋው የአውሮፓ ኅብረት አትላንታ ኦፕሬሽንየባሕር ኃይል፤ ምላሽ ለመስጠት በአቅራቢያው ያለ መርከብ አሠማርቷል። በተጨማሪም የጃፓን አውሮፕላን በአካባቢው የቅኝት በረራ አካሂዷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X