ኬንያ እና ኢትዮጵያ በጤና፣ በትምህርት እና በሴቶች የንግድ ተሳትፎ ዙሪያ ድንበር ተሻጋሪ ስምምነቶች ተፈራረሙ
19:14 07.11.2025 (የተሻሻለ: 19:24 07.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኬንያ እና ኢትዮጵያ በጤና፣ በትምህርት እና በሴቶች የንግድ ተሳትፎ ዙሪያ ድንበር ተሻጋሪ ስምምነቶች ተፈራረሙ
🫱🫲 በኢጋድ የሚደገፈው ስምምነት ሁለቱ ሀገራት በጋራ ድንበራቸው ላይ የሚኖሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት ለመለወጥ የሚያስችል ተልዕኮ ላይ በጋራ እንዲሠሩ ያስችላል ተብሏል፡፡
የድንበር አከባቢዎችን ከእንቅፋት ወደ ድልድይነት በመቀየር የእድል ማዕከላት ማድረግ እንደሚገባ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ወቅት ተጠቁሟል፡፡
በስምምነት ማዕቀፉ መሠረት በድንበር ተሻጋሪ የጤና ጉዳዮች ላይ የሚሠራ የቴክኒክ የሥራ ቡድን በሽታዎችን ለመከታተል፣ ለአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ እና ለድንበር ተሻጋሪ የጤና እንክብካቤ ቅንጅት መጠናከር ይቋቋማል።
በተጨማሪም ለሴት ነጋዴዎች ሥልጠና፣ የብድር አቅርቦት እና ደህንነቱ የተጠበቀ የንግድ ቦታዎችን የሚያቀርብ የተዋሃደ መድረክ ይፈጠራል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X