በክህሎት ኢትዮጵያ ፕሮግራም እስካሁን ከ80 በላይ ቴክኖሎጂዎች መመረታቸው ተገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበክህሎት ኢትዮጵያ ፕሮግራም እስካሁን ከ80 በላይ ቴክኖሎጂዎች መመረታቸው ተገለፀ
በክህሎት ኢትዮጵያ ፕሮግራም እስካሁን ከ80 በላይ ቴክኖሎጂዎች መመረታቸው ተገለፀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 07.11.2025
ሰብስክራይብ

በክህሎት ኢትዮጵያ ፕሮግራም እስካሁን ከ80 በላይ ቴክኖሎጂዎች መመረታቸው ተገለፀ

በፕሮጀክቱ ሥር የተካተቱ ከ500 በላይ ወጣቶች ተኪ ምርቶችን እና የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በሀገር ውስጥ እያመረቱ እንደሚገኙ የፕሮግራሙ አስተባባሪ ብሩክ ሰለሞን ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡

በክህሎት ኢትዮጵያ ሁለተኛ ዙር በተኪ ምርቶች ላይ 152 ወጣቶች 99 ቴክኖሎጂዎችን እያለሙ ነው ብለዋል። በፕሮግራሙ ስር ግብርና፣ ጤና፣ ደህንነት እና አገልግሎትን የሚያሻሽሉ ቴክኖሎጂዎች መሠራታቸውንም ተናግረዋል።

ወጣቶቹ ካበለፀጓቸው የቴክኖሎጂ ውጤቶች መካከል፦

◻ የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ፣

◻ የግብርናና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በሮቦት በመታገዝ ማከናወን የሚያስችል ቴክኖሎጂ፣

◻ የፕላስቲክ ምርቶች ማምረቻ መሳሪያ እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡

የፕሮግራሙ አስተባባሪ በኢትዮጵያዊያን የተመረቱ ቴክኖሎጂዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ በተካሄዱ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ውድድሮች ላይ ተሸላሚ መሆን መቻላቸውንም አስታውሰዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0