የዩክሬንን ግጭት ለመፍታት በሚደረገው ጥረት መሻሻል ታይቷል - ትራምፕ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየዩክሬንን ግጭት ለመፍታት በሚደረገው ጥረት መሻሻል ታይቷል - ትራምፕ
የዩክሬንን ግጭት ለመፍታት በሚደረገው ጥረት መሻሻል ታይቷል - ትራምፕ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 07.11.2025
ሰብስክራይብ

የዩክሬንን ግጭት ለመፍታት በሚደረገው ጥረት መሻሻል ታይቷል - ትራምፕ

"ጦርነቱ እንዲያበቃ እንፈልጋለን። ያ ጦርነት አብቅቶ ብናይ ደስ ይለናል" ሲሉ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት በኋይት ሀውስ ከአምስት የመካከለኛው እስያ ሀገራት መሪዎች ጋር ባደረጉት ስብሰባ ላይ ተናግረዋል።

በዩክሬን የጸጥታ ፕሮቶኮሎች ዙሪያ አሁንም መስማማት እንደሚያስፈልግ ያነሱት የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ፤ ግጭቱ ይፈታል ሲሉ በትናንትናው ዕለት ገልፀዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ ሩሲያ እና አሜሪካ በዩክሬን ግጭት ላይ ያላቸውን አቋም ለማቀረራብ እና በቡዳፔስት በፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና በአሜሪካ አቻቸው ዶናልድ ትራምፕ መካከል ስብሰባ ለማድረግ ጥቂት ጉዳዮችን መፍታት አለባቸው ሲሉ የሃንጋሪው ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን ተሰምተዋል።

"እነዚህ ጉዳዮች ከተፈቱ በቀናት ውስጥ በቡዳፔስት የሰላም ጉባኤ ማካሄድ ይቻላል፤ በዚህም በተሳታፊ ወገኖች ስምምነት ላይ በመመስረት የተኩስ አቁም ሊታወጅ እና ሰላም ወደ ዩክሬን ሊመጣ ይችላል" ብለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0