በኢትዮጵያ ባለፈው የእርሻ ወቅት ከ32 ሺህ በላይ የካካዎ ችግኞች ለአርሶ አደሮች ተከፋፍለዋል - የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበኢትዮጵያ ባለፈው የእርሻ ወቅት ከ32 ሺህ በላይ የካካዎ ችግኞች ለአርሶ አደሮች ተከፋፍለዋል - የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት
በኢትዮጵያ ባለፈው የእርሻ ወቅት ከ32 ሺህ በላይ የካካዎ ችግኞች ለአርሶ አደሮች ተከፋፍለዋል - የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት - Sputnik አፍሪካ, 1920, 07.11.2025
ሰብስክራይብ

በኢትዮጵያ ባለፈው የእርሻ ወቅት ከ32 ሺህ በላይ የካካዎ ችግኞች ለአርሶ አደሮች ተከፋፍለዋል - የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት

ሀገሪቱ ለም መሬቶቿን፣ ምቹ የአየር ንብረት እና በቂ ዝናቧን በመጠቀም እና የካካዎ ኢንዱስትሪን በማልማት ወደ ዓለም አቀፉ የቸኮሌት ገበያ ለመግባት እየሠራች እንደምትገኝ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ንጉሴ ደቻሳ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

በቴፒ ብሔራዊ ቅመማ ቅመም ምርምር ማዕከል የተዋወቀው የፎራስተሮ ዓይነት ካካዎ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያ ዝርያ በመሆን መመዝገቡ ይታወሳል፡፡

ኢትዮጵያ በራሷ የካካዎ ምርት ቸኮሌት እያመረተች መሆኗን ማስታወቋ ይታወሳል፡፡

አፍሪካ ከዓለም አቀፍ የካካዎ ምርት 70 በመቶውን እንደምትሽፍን የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ድርጅት መረጃ ያመላክታል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0