ባሌ ተራሮች፣ ቦረና እና ጋምቤላ ብሔራዊ ፓርኮች በአህጉር ደረጃ ወሳኝ ጥበቃ ከሚደረግላቸው ሥፍራዎች ዝርዝር ውስጥ ተካተቱ
11:52 07.11.2025 (የተሻሻለ: 12:04 07.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ባሌ ተራሮች፣ ቦረና እና ጋምቤላ ብሔራዊ ፓርኮች በአህጉር ደረጃ ወሳኝ ጥበቃ ከሚደረግላቸው ሥፍራዎች ዝርዝር ውስጥ ተካተቱ
የአፍሪካ የዱር እንስሳት ፋውንዴሽን የአህጉሪቱ ቁልፍ አካባቢዎች አጋርነት ተነሳሽነትን ያስጀመረ ሲሆን ከ33 ሀገራት ለተመረጡ 162 አካባቢዎች ጥበቃ እንደሚደረግላቸው አስታወቋል፡፡
ይህ ተነሳሽነት በቦትስዋና ጋቦሮኔ በተካሄደውና የብዝሃ ሕይወት የጋራ ሰነድን በማጽደቅ በተጠናቀቀው የመጀመሪያው የአፍሪካ የብዝሃ ሕይወት ጉባኤ ላይ ይፋ ተደርጓል፡፡
በመድረኩ ኢትዮጵያ በሥነ-ምህዳር ቱሪዝም ያደረገችው ጥረት ማህበረሰብን የብዝሃ ሕይወት ጥበቃ ተጠቃሚ የሚያደርግ ሆኖ በማሳየነት ቀርቧል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

