ሳፋሪኮም የግማሽ ዓመት ትርፉ በ55 በመቶ መጨመሩን አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሳፋሪኮም የግማሽ ዓመት ትርፉ በ55 በመቶ መጨመሩን አስታወቀ
ሳፋሪኮም የግማሽ ዓመት ትርፉ በ55 በመቶ መጨመሩን አስታወቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 06.11.2025
ሰብስክራይብ

ሳፋሪኮም የግማሽ ዓመት ትርፉ በ55 በመቶ መጨመሩን አስታወቀ

የኬንያው ግዙፍ የቴሌኮም ኩባንያ የኢትዮጵያ ኦፕሬሽን ኪሳራው በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነሱ እና በሀገር ውስጥ ገበያ ያለው የተረጋጋ ዕድገት ለትርፉ መጨመር መነሻ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ኩባንያው እስከ መስከረም ወር ባሉት ስድስት ወራት ውስጥ 65.2 ቢሊዮን የኬንያ ሺሊንግ (506 ሚሊዮን ዶላር) የሥራ ትርፍ አስመዝግቧል። በኢትዮጵያ የደረሰበት ኪሳራ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ59 በመቶ ቀንሷል።

የቡድን የአገልግሎት ገቢም ጤናማ ዕድገት አሳይቶ 199.9 ቢሊዮን ሺሊንግ (1.5 ቢሊዮን ዶላር) ደርሷል። ለዚህ ዕድገት ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረከተው የሳፋሪኮም የሞባይል የፋይናንስ አገልግሎት የሆነው ኤም-ፔሳ ሲሆን ገቢውም 88.1 ቢሊዮን ሺሊንግ (681.9 ሚሊዮን ዶላር) ሆኖ ተመዝግቧል።

በኢትዮጵያ የታየው የተሻለ አፈጻጸም ሳፋሪኮም ለወደፊት በሀገሪቱ ተደራሽነቱን ለማስፋት እና ለውድድር ክፍት በተደረገው ገበያ ላይ ተስፋ እንዲጥል አዎንታዊ እርምጃ መሆኑ ተዘግቧል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0