ኢትዮጵያ በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ስር የታሪፍ ቅነሳ የሚደረግላቸው ሀገራትን ዝርዝር ይፋ አደረገች
19:46 06.11.2025 (የተሻሻለ: 19:54 06.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ስር የታሪፍ ቅነሳ የሚደረግላቸው ሀገራትን ዝርዝር ይፋ አደረገች
የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ግብፅን ጨምሮ በቀጣናዊ የገበያ ትስስሩ ለታሪፍ ቅናሹ ብቁ የሆኑ 24 የአፍሪካ ሀገራት ይፋዊ ዝርዝርን ለሁሉም የጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች እና ለጉምሩክ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማትና አስተዳደር ማዕከል ባሰራጨው ሰርኩላር ደብዳቤ ላይ አስታወቋል፡፡
ከፀደቁት አባል ሀገራት በሚመጡ እቃዎች ላይ ውሳኔ የተደረሰበትን የታሪፍ ቅናሽ ተግባራዊ ማድረግ እንዲጀመር መመሪያ ሰጥቷል።
የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 574/2025 መሠረት በማድረግ ያሳለፈው ውሳኔ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
ከምስራቅ አፍሪካ ሰባት ሀገራት፣
ከደቡብ አፍሪካ ስምንት ሀገራት፣
ከሰሜን አፍሪካ አራት ሀገራት፣
ከምዕራብ አፍሪካ ሦስት ሀገራት፣
ከመካከለኛው አፍሪካ ካሜሩን ይገኙበታል፡፡
ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጠና ስር መስከረም 29፣ 2018 በይፋ ግብይት መጀመሯ የሚታወስ ነው፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X