የአሜሪካ ፍርድ ቤት ቦይንግ ላይ ሊቀርብ የነበረው የወንጀል ክስ ጉዳይ እንዲነሳ ወሰነ
19:26 06.11.2025 (የተሻሻለ: 09:04 07.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአሜሪካ ፍርድ ቤት ቦይንግ ላይ ሊቀርብ የነበረው የወንጀል ክስ ጉዳይ እንዲነሳ ወሰነ
የዩናይትድ ስቴትስ ዳኛ፤ የሀገሪቱ ፍትሕ ሚኒስቴር በአወሮፕላን አምራቹ ላይ የቀረበው የወንጀል ክስ ውድቅ እንዲደረግ ያቀረበውን ጥያቄ ሐሙስ ዕለት አጽድቀዋል፡፡
በዚህም ከስድስት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ እና ኢንዶኔዥያ በቦይንግ የበረራ መቆጣጠሪያ ሥርዓት (ኤምካስ) ምክንያት ሁለት የ737 ማክስ አውሮፕላኖች ተከስክሰው 346 ሰዎች ለተገደሉበት አደጋ ከወንጀል ተጠያቂነት ማምለጥ ችሏል ሲሉ ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡
የፍትሕ መሥሪያ ቤቱን ጥያቄ ያፀደቁት የቴክሳስ ዳኛ፤ ጉዳዩን ውድቅ ማድረግ የሕዝብን ጥቅም የሚጠብቅ ነው የሚለውን መከራከሪያ ውድቅ በማድረግ፤ ጥያቄውን ለመግፋት ግን ሥልጣን እንደሌላቸው ገልፀዋል ነው የተባለው፡፡
መንግሥት ከቦይንግ ጋር የደረሰው ስምምነት "ለአወሮፕላን ተጠቃሚው ሕዝብ ደህንነት ሲባል አስፈላጊውን ተጠያቂነት ማረጋገጥ አልቻለም" ብለዋል።
የአሜሪካ መንግሥት ቦይንግ ተሻሽሏል ሲል፤ የፌዴራል አቪዬሽን አስተዳደርም ኩባንያው ላይ የተጠናከረ ቁጥጥር እያደረገ እንደሆነ ይገልጻል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X