የአፍሪካ ሀገራት ለቴክኖሎጂ ኢንቨስትመንት ምቹ ምሕዳር መፍጠር አለባቸው - አምባሳደር ሙሉ ሰሎሞን

ሰብስክራይብ

የአፍሪካ ሀገራት ለቴክኖሎጂ ኢንቨስትመንት ምቹ ምሕዳር መፍጠር አለባቸው - አምባሳደር ሙሉ ሰሎሞን

በጀርመን የቀድሞ የኢትዮጵያ አምባሳደር፤ ባለሐብቶች ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል በሚፈጥሩ የቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ እንዲሠማሩ ምቹ አሠራሮችን ተግባራዊ ማድረግ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

"እያንዳንዱ የአፍሪካ ሀገር ለኢንቨስትመንት፣ ንግድ እና የዕውቀት ሽግግር ያለውን ተመራጭነት በደምብ አውጥቶ ማሳየት አለበት። ይህም አኅጉሪቱ ቴክኖሎጂን በመጠቀም እሴት የተጨመረባቸው ምርቶቸን በስፋት ወደ ውጭ ለመላክ ያግዛታል" ብለዋል።

አምባሳደሯ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ የአፍሪካን የኢንቨስትመንት አቅም ለማጎልበት ሊተኮርባቸው ይገባል ያሏቸውን ሌሎች ጉዳዮችም አንስተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0