ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ ለሁለተኛው የኃይል ትስስር ፕሮጀክት ዝርጋታ ስምምነት ተፈራረሙ
18:34 06.11.2025 (የተሻሻለ: 18:44 06.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ ለሁለተኛው የኃይል ትስስር ፕሮጀክት ዝርጋታ ስምምነት ተፈራረሙ
የኢትዮጵያን ጋላፊ ማከፋፈያ ጣቢያ ከጅቡቲው ናጋድ ማከፋፈያ ጣቢያ ጋር በሚያገናኘው በዚህ ፕሮጀክት፤ የ230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ግንባታ እንደሚከናወን በጅቡቲ በተካሄደው የፊርማ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገልጿል፡፡
በጅቡቲ ግዛት የሚዘረጋውን 190 ኪሎ ሜትር ጨምሮ በአጠቃላይ 292 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነውን የኃይል መስመር ፕሮጀክት በ18 ወራት ለማጠናቀቅ እቅድ ተይዟል፡፡
ዓለም ባንክ ዝርጋታውን በ55 ሚሊዮን ዶላር ብድር የሚደግፈው ሲሆን የግንባታ ውሉ ትራንስሬይል ሊሚትድ ለተሰኘ የህንድ ኢንጂነሪንግ ኩባንያ መሰጠቱ ተጠቁሟል፡፡
“ፕሮጀክቱ ታዳሽ የኃይል ሀብቶችን በመጠቀም ላይ የተመሠረተ ብሔራዊ የኃይል ፖሊሲ እንድንተገብር ይረዳናል፣ ይህም 100 በመቶ የንጹህ ኃይል ግባችንን እንድናሳካ ያስችለናል” ሲሉ የጅቡቲ የኢነርጂ እና የተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትር ዮኒስ አሊ ጉዲ ተናግረዋል።
የኃይል መስመር ዝርጋታው የጅቡቲ እና ኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ የኃይል ትብብር አካል ሆኖ እ.አ.አ በ2013 የተጠነሰሰ ፕሮጀክት ነው፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X