የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የ2.8 ቢሊዮን ብር የውሃ ፕሮጀክቶችን ለመገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የ2
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የ2 - Sputnik አፍሪካ, 1920, 06.11.2025
ሰብስክራይብ

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የ2.8 ቢሊዮን ብር የውሃ ፕሮጀክቶችን ለመገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ

በኦሮሚያ ክልል በዋጪሌ፣ ኤልወያ እና ዳሮላቡ አካባቢዎች እንዲሁም በተለያዩ ወረዳዎች የጉድጓድ ቁፋሮ የሚከናወኑባቸው ዋና ዋና የመጠጥ ውሃና የንፅህና መጠበቂያ ፕሮጀክቶችን መገንባትን የሚያካትት ነው፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ አስፋው ዲንጋሞ (ዶ/ር)፤ ኩባንያዎቹ ሁሉንም ሥራ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ እንዲያጠናቅቁ እና በስምምነቶቹ መሠረት ከፍተኛውን የጥራት ደረጃ እንዲጠብቁ አሳስበዋል፡፡

ይህን ፕሮጀክት ለማስፈፀም በድምሩ አስራ ሁለት የተለያዩ የውል ስምምነቶች ከተለያዩ ተቋራጮች ጋር ተፈርመዋል፡፡

ሥራዎቹ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ተጠናቅቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ ውል መገባቱን ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0