የሩሲያ ነፃ የትምህርት ማዕከል በቡርኪና ፋሶ ተመረቀ
16:55 06.11.2025 (የተሻሻለ: 17:04 06.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሩሲያ ነፃ የትምህርት ማዕከል በቡርኪና ፋሶ ተመረቀ
ይፋዊ ሥነ-ሥርዓቱ ኡጋዱጉ በሚገኘው የሩሲያ ሳይንስና ባሕል ማዕከል ግቢ ውስጥ ተካሂዷል፡፡
በሩሲያ እና በቡርኪና ፋሶ መካከል አዲስ የትምህርት ድልድይ በመሆን ጥራት ያለው የሩሲያ ትምህርት ለማግኘት ለሚመኙ የበቁ የሀገሪቱ ወጣቶች የተበረከተ ነው ሲሉ አዘጋጆቹ ገልፀዋል፡፡
በሀገሪቱ ውስጥ በተለያዩ ዘርፎች የሚሠሩ የሩሲያ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች እና ሌሎችም የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓቱን ታድመዋል፡፡
ማዕከሉ የሩሲያ ደቡብ ኡራል ስቴት ፔዳጎጂካል ዩኒቨርሲቲ ተቀጥላ ሲሆን የቡርኪና ፋሶ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ሚኒስትር ቡባካር ሳቫዶጎ እና ከሁለቱም ሀገራት የተውጣጡ በርካታ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በተገኙበት ተመርቋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X