ኢትዮጵያ ባለፉት ሶስት ወራት 300 ድሮኖች ማምረቷ ተገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ ባለፉት ሶስት ወራት 300 ድሮኖች ማምረቷ ተገለፀ
ኢትዮጵያ ባለፉት ሶስት ወራት 300 ድሮኖች ማምረቷ ተገለፀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 06.11.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ ባለፉት ሶስት ወራት 300 ድሮኖች ማምረቷ ተገለፀ

ድሮኖቹ በስካይዊን እና ኤሮአባይ ፋብሪካዎች የጋራ ጥረት መገንባታቸውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዳንኤል ጉታ፤ ለፓርላማ የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሩቡን ዓመት ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ተናግረዋል፡፡

በሁለቱም ኩባንያዎች በቅርብ ጊዜ የተመረቱት ድሮኖች በዋናነት ለመዝናኛና ገቢ ማስገኛነት የሚውሉ እና የሀገር ውስጥና የቀጣናዊ ገበያዎችን ዒላማ ያደረጉ መሆናቸውን ገልፀዋል።

በመቶዎች የሚቆጠሩ ተጨማሪ ድሮኖች በመመረት ላይ መሆናቸውን የጠቆሙት ም/ዳይሬክተሩ፤ የምርት አቅምን ለማሳደግ የጥሬ ዕቃ ክፍተቶችን ለመሙላት ጥረቶች እየተደረጉ መሆናቸውን አመላክተዋል።

በሀገር ውስጥ የተሠሩ ድሮኖች ከዚህ ቀደም በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ምረቃ እና በኢሬቻ በዓል ወቅት ጥቅም ላይ መዋላቸውን የሀገር ውስጥ ሚዲያ በዘገባው አስታወሷል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0