የአፍሪካ መሪዎች የአህጉሪቱን የተፈጥሮ ሃብት ወደ ዘላቂ ብልጽግና ሊቀይሩ ይገባል - የቦትስዋና ፕሬዝዳንት
15:49 06.11.2025 (የተሻሻለ: 16:04 06.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአፍሪካ መሪዎች የአህጉሪቱን የተፈጥሮ ሃብት ወደ ዘላቂ ብልጽግና ሊቀይሩ ይገባል - የቦትስዋና ፕሬዝዳንት
የብዝሃ ሕይወት የአፍሪካ አህጉር ብሔራዊ ሃብት ወሳኝ አካል እንጂ የቅንጦት አይደለም ሲሉ ዱማ ጊዴዎን ቦኮ በጋቦሮኔ፣ ቦትስዋና በተካሄደው የመጀመርያው የአፍሪካ የብዝሃ ሕይወት ጉባኤ ላይ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡
“ብልጽግና በጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ብቻ ሳይሆን ደህንነቱ በተጠበቀ የምግብ ስርዓት፣ ንጹህ ውሃ፣ መቋቋም በሚችል ማህበረሰብ እና ጤናማ ሥነ-ምህዳሮች መገለፅ አለበት” ብለዋል፡፡
40 በመቶ የሚሆነው መሬት ጥበቃ የሚደርግበትን የቦትስዋና ሞዴል ለአህጉሪቱ ምሳሌ አድርገው አቅርበዋል፡፡
የብዝሃ ሕይወት መጥፋት የማህበረሰብን ደህንነት በቀጥታ እንደሚያሰጋ ያስጠነቀቁት ፕሬዝዳንት ቦኮ፤ የገንዘብ ድጋፍ ክፍተቶችን ለመሙላት የአፍሪካ የብዝሃ ሕይወት ፈንድ እንዲቋቋም ሐሳብ አቅርበዋል፡፡
“ይህ ጉባኤ ከቃላት በላይ ይሁን። የለውጥ መነሻ ይሁን” በማለት፤ የሥነ-ምህዳር ጤና እና የኢኮኖሚ ልማት አብረው የሚዳብሩበትን የወደፊት ጊዜ ለመገንባት የተባበረ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia
/ 

