ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የሁለትዮሽ የገበያ ዕድል ድርድር ስምምነት ቀጣይ ሳምንት ሊፈራረሙ ነው

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ እና ሩሲያ የሁለትዮሽ የገበያ ዕድል ድርድር ስምምነት ቀጣይ ሳምንት ሊፈራረሙ ነው
ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የሁለትዮሽ የገበያ ዕድል ድርድር ስምምነት ቀጣይ ሳምንት ሊፈራረሙ ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 06.11.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የሁለትዮሽ የገበያ ዕድል ድርድር ስምምነት ቀጣይ ሳምንት ሊፈራረሙ ነው

ሞስኮ በሚካሄደው የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ላይ የሚፈረመው ይህ ሰነድ፤ የኢትዮጵያን የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት በታለመው ጊዜ ለማሳካት እገዛ እንደሚያደርግ የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

ባለሥልጣኑ ከሩሲያ ፕሬዝዳንታዊ ሥራ አስፈፃሚ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ማክሲም ኦሬሽኪን እና ከሩሲያ አቻቸው ማክሲም ሬሼንኮቭ ጋር በሁለቱ ሀገራት ንግድና ኢኮኖሚያዊ ትስስሮች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት ማካሄዳቸውን አስታውቀዋል።

“በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የንግድ ግንኙነት ካለን የሕዝብ ብዛት፣ ኢኮኖሚና ታሪካዊ ግንኙነት አንጻር ሲታይ ገና ብዙ መሥራት እንዳለብን የሚያሳይ መሆኑን የጋራ መግባባት ላይ ደርሰናል። ወደፊትም የኢትዮጵያን ምርቶች በጥራትና በብዛት ወደ ሩሲያ ገበያ ለመላክ ያለንን ዕምቅ አቅም አስረድቻለሁ” ብለዋል፡፡

የሩሲያ ኩባንያዎች በኢ-ንግድና አውቶሞቢል ዘርፍ በትብብር ለመሥራት ፍላጎት እንዳላቸው መግለፃቸውንም ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0