ኔቶ ካሊኒንግራድ ክልልን የመዝጋት ወታደራዊ ልምምድ እያካሄደ ነው - የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
14:23 06.11.2025 (የተሻሻለ: 14:24 06.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኔቶ ካሊኒንግራድ ክልልን የመዝጋት ወታደራዊ ልምምድ እያካሄደ ነው - የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
"ባልቲክን ያለማቋረጥ ወታደራዊ የማድርገ ሂደት አለ፤ የጥምር ኃይሎችና መሳሪያዎችም እየተጨመሩበት ነው" ሲሉ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምክትል ኃላፊ አሌክሳንደር ግሩሽኮ ለሩሲያ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።
ባልቲክ ከረጅም ጊዜ ጀምሮ ክልላዊ ችግሮች በሰላማዊ መንገድ የሚፈቱበት ሁለገብ የውጤታማ ትብብር አካባቢ ነበር ሲሉም አክለዋል።
"በአሁኑ ጊዜ፤ በኔቶ አባል ሀገራት ምክንያት ይህ የአውሮፓ ክፍል ወደ ግጭት ቀጣና ተቀይሯል፤ ይህም ፊንላንድ እና ስዊድን በመቀላቀላቸው ምክንያት በከፍተኛ ሁኔታ ተባብሷል።"
◻ ጥምረቱ በዚህ ዓመት በጀመረው የባልቲክ ሴንትሪ ተልዕኮ በውሃ አካባቢው የራሱን የአሰሳ ደንቦች ለመመስረት እየሞከረ ነው። የኔቶ አጋሮች የሩሲያን የባሕር ጭነት ትራንስፖርት መቆጣጠር፣ ከዚያም በተቻለ መጠን መገደብ ይፈልጋሉ ሲሉ ግሩሽኮ አመልክተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X