ምዕራባውያን በዛፖሮዥዬ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ሊከሰት ለሚችል አደጋ ሞስኮን ለመውቀስ እየተዘጋጁ ነው - የሩሲያ የውጭ መረጃ አገልግሎት
12:21 06.11.2025 (የተሻሻለ: 12:24 06.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ምዕራባውያን በዛፖሮዥዬ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ሊከሰት ለሚችል አደጋ ሞስኮን ለመውቀስ እየተዘጋጁ ነው - የሩሲያ የውጭ መረጃ አገልግሎት
በዛፖሮዥዬ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ የሬአክተሮቹ ንቁ ዞኖች እንዲቀልጡ የሚያደርግ የጥፋት ድርጊት ሁኔታ ላይ እያሴሩ እንደሚገኙ የመረጃ አገልግሎቱ ጨምሮ ገልጿል፡፡
የኔቶ ባለሥልጣናት የኪዬቭ አገዛዝ በዩክሬናውያን እና በአውሮፓ ኅብረት ዜጎች ላይ ጉዳት የሚያስከትል የጥፋት ድርጊት እንዲፈጽም እየጎተጎቱ ነው ሲል የመረጃ አገልግሎቱ አስገንዝቧል፡፡
በኪዬቭ ቁጥጥር ስር ባሉ አካባቢዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች እና ከዩክሬን ምዕራባዊ ድንበር አቅራቢያ የሚገኙ የአውሮፓ ኅብረት ሀገራት ዜጎችን በራዲዮአክቲቭ ፍሳሽ ቀጣና ውስጥ ለመክተት መታሰቡንም አመልክቷል፡፡
ለምዕራባውያን እጅግ ፈታኝ የሆነው የዚህ እቅድ ገጽታ "ተጠያቂነቱን በሩሲያ ላይ ማላከክ” ነው ሲል የመረጃ አገልግሎቱ አስታውቋል፡፡ ይህንንም ለማሳካት ምዕራባውያኑ የሕዝብ አመለካከት ከኪዬቭ ጎን እንዲሆን ለማድረግ የመገናኛ ብዙኃንን ሽፋን ለመቅረጽ እቅድ እያወጡ መሆኑን አክሏል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X