አማፂው የፈጥኖ ደራሽ ኃይል በደቡባዊ ሱዳን ከተማ በሰነዘረው ጥቃት ከ40 በላይ ሰዎች ተገደሉ
11:43 06.11.2025 (የተሻሻለ: 11:44 06.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
አማፂው የፈጥኖ ደራሽ ኃይል በደቡባዊ ሱዳን ከተማ በሰነዘረው ጥቃት ከ40 በላይ ሰዎች ተገደሉ
የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በሰሜን ኮርዶፋን ግዛት ውስጥ በምትገኘው ባራ ከተማ ላይ ድብደባ ፈፅሞ ቢያንስ 37 ሰዎች ቆስለዋል ሲል የአካባቢውን የሰብዓዊ እርዳታ ኮሚሽን ጠቅሶ የአረብ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል፡፡
አማፂ ቡድኑ ለ18 ወራት ሲካሄድ ከቆየ ውጊያ በኋላ በሰሜን ዳርፉር የመንግሥት ዋነኛ ይዞታ በሆነችው ኤል ፋሸር ከተማ የሱዳን ጦር 6ኛ እግረኛ ክፍለ ጦር ዋና መምሪያን እንደተቆጣጠረ ጥቅምት 16 አስታውቋል።
የሱዳን ጦር ጠቅላይ አዛዥ አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን ወታደሮች ከከተማዋ መውጣታቸውን ባሳለፍነው ማክሰኞ አረጋግጠዋል።
ሞስኮ በኤል ፋሸር ሪፖርት በተደረጉ የጅምላ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ዙሪያ ጥልቅ ስጋቷን ገልጻ፤ በሚያዝያ 2023 የጀመረው ግጭት በሰላማዊ መንገድ መፈታቱን እንደምትደግፍ ጠቁማለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X