ኢትዮጵያ በአበባ ልማት ዘርፍ ከ60 ሺህ በላይ የሥራ ዕድል መፍጠር ችላለች ተባለ
20:12 05.11.2025 (የተሻሻለ: 20:14 05.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በአበባ ልማት ዘርፍ ከ60 ሺህ በላይ የሥራ ዕድል መፍጠር ችላለች ተባለ
የአትክልትና ፍራፍሬ ዘርፍ ደግሞ ለ200 ሺህ ገደማ ሰዎች ሥራ ማስገኘቱን የኢትዮጵያ አትክልትና ፍራፍሬ አምራቾችና ላኪዎች ማህበር ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ዘውዴ ተናግረዋል፡፡
በሁለቱም ዘርፎች ባለው የሰው ኃይል ስብጥር ሴቶች ከ75 በመቶ እስከ 80 በመቶ የሚሆነውን የሥራ ድርሻ ይይዛሉ ብለዋል።
የኢትዮጵያ አትክልትና ፍራፍሬ ዘርፍ የወጪ ንግድ በዓመት ግማሽ ቢሊዮን ዶላር እንደሚገመት በማንሳት፤ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ ያለውን ሚናም አጉልተው አንስተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X