የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ሩሲያ በኢትዮጵያ ኢንቨስት የምታደርግባቸውን ዘርፎች እንድታሰፋ ጥሪ አቀረቡ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ሩሲያ በኢትዮጵያ ኢንቨስት የምታደርግባቸውን ዘርፎች እንድታሰፋ ጥሪ አቀረቡ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ሩሲያ በኢትዮጵያ ኢንቨስት የምታደርግባቸውን ዘርፎች እንድታሰፋ ጥሪ አቀረቡ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 05.11.2025
ሰብስክራይብ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ሩሲያ በኢትዮጵያ ኢንቨስት የምታደርግባቸውን ዘርፎች እንድታሰፋ ጥሪ አቀረቡ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከሩሲያ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንታዊ ሥራ አስፈፃሚ ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ማክሲም ኦሬሽኪን እና ከሩሲያ የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ማክሲም ሬሼትኒኮቭን ጋር ተገናኝተው በስትራቴጂካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

“ሩሲያ በተለያዩ የትብብር ዘርፎች ለኢትዮጵያ ለምታደርገው ቀጣይነት ያለው ድጋፍ አድናቆት አለን፡፡ በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ እና በማዕድን ልማት እንዲሁም በማዳበሪያ ምርት፣ በብረታ ብረት ኢንዱስትሪ እና የኒውክሌር እና ታዳሽ ኃይል ፕሮጀክቶችን ጨምሮ በኃይል መሠረተ ልማት፤ ለሩሲያ ኢንቨስትመንት እና የጋራ ትብብር ጥሪ እናቀርባለን” ብለዋል፡፡

▫ እነዚህ የሁለትዮሽ ግንኙነቶች በዘላቂ ልማት፣ በቀጣናዊ ደህንነት እና በጋራ ብልጽግና ላይ በማተኮር የኢትዮጵያ-ሩሲያ አጋርነትን ወደ አዲስ የስትራቴጂካዊ ትብብር ደረጃ ለማሳደግ ማሳያ ናቸው ሲል ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በማህበራዊ ገጹ አስታውቋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0