ኢትዮጵያና ቻይና የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት የሁለትዮሽ የገበያ ድርድር ተፈራረሙ
17:52 05.11.2025 (የተሻሻለ: 17:54 05.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያና ቻይና የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት የሁለትዮሽ የገበያ ድርድር ተፈራረሙ
ኢትዮጵያ ድርጅቱን ለመቀላቀል በምታደርገው ሂደት ውስጥ ጉልህ እርምጃ ነው የተባለው ይህ ስምምነት በጄኔቫ መፈረሙን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ስምምነቱ የሁለቱን ሀገራት የኢኮኖሚ ትብብር ለማጥበቅ እና ፍትሐዊ፣ ሁሉን አቀፍና በሕግ ላይ የተመሠረተ ዓለም አቀፍ የንግድ ስርዓት ለማስፋፋት ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት የሚያንፀባርቅ ነው ተብሏል፡፡
ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን በምታደርገው ጥረት በቅርቡ ከቱርክዬ እና አርጀንቲና ጋር የሁለትዮሽ የገበያ ድርድር መፈራረሟ ይታወሳል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X