“በከፍተኛ ችግር ወቅት እኛን ለመታደግ የመጣችው ሩሲያ ናት” - የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ“በከፍተኛ ችግር ወቅት እኛን ለመታደግ የመጣችው ሩሲያ ናት” - የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት
“በከፍተኛ ችግር ወቅት እኛን ለመታደግ የመጣችው ሩሲያ ናት” - የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት - Sputnik አፍሪካ, 1920, 05.11.2025
ሰብስክራይብ

“በከፍተኛ ችግር ወቅት እኛን ለመታደግ የመጣችው ሩሲያ ናት” - የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት

ፕሬዝዳንት ፋውስቲን-አርሻንዥ ቱዋዴራ ሀገራቸው ከሞስኮ ጋር ያላት ግንኙነት "የወዳጅነትና ወንድማማችነት" ነው ሲሉ ገልጸውታል።

በ2009 ዓ.ም የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የመከላከያ ኃይሎች የጦር መሳሪያ ሲያስፈልጋቸው፤ ሩሲያ "በነጻ" ለማቅረብ የተስማማች ብቸኛ ሀገር እንደነበረች ቱዋዴራ ከፈረንሳይ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ አስታውሰዋል።

የሩሲያ አሠልጣኞች በጦር መሳሪያዎቹ አጠቃቀም ላይ የሀገሪቱን ወታደሮች እንዲያሠለጥኑ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ፈቃድ መስጠቱንም አንስተዋል።

በተጨማሪም እ.ኤ.አ በ2020-2021 በሀገሪቱ ጥምረት የፈፀሙት 'የለውጥ አርበኞች ቅንጅት' አማፂያን ከፍተኛ ጥቃት በፈጸሙበት ወቅት ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ከጦር ኃይሏ ጉድለቶች የተነሳ እርዳታ ለማግኘት "ሁሉንም አካላት ተማጽና ነበር" ሲሉ ቱዋዴራ አስረድተዋል።

"ሩዋንዳ እና ሩሲያ ብቻ በአዎንታዊ መልኩ ምላሽ ሰጥተዋል" ብለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0