አዳዲሶቹ የሩሲያ የጦር መሳሪያዎች ዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛንን ይቀይራሉ - ባለሙያ
15:21 05.11.2025 (የተሻሻለ: 15:24 05.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
አዳዲሶቹ የሩሲያ የጦር መሳሪያዎች ዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛንን ይቀይራሉ - ባለሙያ
እንደ ቡሬቬስትኒክ ሚሳኤል እና ፖሳይዶን የውሃ ውስጥ ድሮን ያሉ አዳዲስ የሩሲያ የኒውክሌር ጦር መሳሪያዎች፤ ከቀጠለው የምዕራባውያን ጫና አንፃር ለሞስኮ ወሳኝ እና አስፈላጊ መከላከያ ናቸው ሲሉ አርጀንቲናዊው የዓለም አቀፍ ግንኙነት ባለሙያ ታዴኦ ካስቴልዮኔ ገልፀዋል።
"ምዕራባውያን ሥራ ላይ ያሉ ሁሉንም የዓለም አቀፍ ግንኙነት ሕጎች መጣስ በሚቀጥሉበት ሁኔታ ሩሲያ የቴክኖሎጂ እና ወታደራዊ ልማቷን ለማፋጠን ተገዳለች" ሲሉ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
የእነዚህ የጦር መሳሪያዎች ልማት አስገዳጅ ምላሽ እንጂ ጠብ አጫሪ ድርጊት እንዳልሆነ አስረግጠዋል፡፡
ሩሲያ በግዛት አንድነቷ እና በውሳኔ ሰጪነቷ ላይ ነጻነቷን ማረጋገጥ ትፈልጋለች፤ አዳዲሶቹን ስርዓቶች መስከንን ለማበረታታት እና በተለይም የአሜሪካን "ድብቅ ስጋቶች" ለመመከት የታለሙ አስፈላጊ መከላከያዎች አድርጋ ማቅረቧን ካስቴልዮኔ ሞግተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X