ምርታማነትን የሚያሳድጉ የተሻሻሉ የበቆሎ ዝርያዎችን ለአርሶ አደሩ እያቀረብን ነው - ብሔራዊ የበቆሎ ምርምር ተቋም

ሰብስክራይብ

ምርታማነትን የሚያሳድጉ የተሻሻሉ የበቆሎ ዝርያዎችን ለአርሶ አደሩ እያቀረብን ነው - ብሔራዊ የበቆሎ ምርምር ተቋም

በሀገሪቱ የበቆሎ ምርታማነትን ለማሳደግ አርሶ አደሩ የተሻሻሉ ዘሮች የስልተ ምርት መመሪያዎችን በአግባቡ መተግበር እንዳለበት፤ በተቋም የበቆሎ ተመራማሪ የሆኑት ቢተው ጥላሁን (ዶ/ር) ይናገራሉ።

ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ በኢትዮጵያ እስከ 2.5 ሚሊየን ሄክታር መሬት በበቆሎ እንደሚሸፈን በማንሳት፤ ሰብሉ ለምግብ ዋስትና መረጋገጥ የላቀ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ገልጸዋል።

"በተለይ በገጠሩ አካባቢ በቆሎን በእንጀራ እና በተለያዩ መልኮች የማይመገብ የለም። ከዚያም ባሻገር ከበቆሎ ባሕላዊ መጠጦች ይዘጋጃሉ፣ ለእንስሳት መኖ እና ለማገዶነትም ያገለግላል" ብለዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0