#viral | ውሻ ከጠባቂነት ወደ አገልጋይነት

ሰብስክራይብ

#viral | ውሻ ከጠባቂነት ወደ አገልጋይነት

በቻይና የተሠራው ይህ አምሳለ ውሻ ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ውጤት፤ የቤት ውስጥ ረዳት ሆኖ ያገለግላል።

ነገሮችን ለመለየት እና ፎቶ ለማንሳት ካሜራ የተገጠመለት ይህ ‘ሮቨር ኤክስ1’ የተሰኘው የሮቦት ውሻ በዙሪያው ያለውን እንቅስቃሴ "ያገናዝባል"። በዚህም አምሳለ ውሻው የቤት ውስጥ ረዳት፣ ጠባቂ አልያም ታማኝ የሮቦት ጓደኛ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል።

የላይኛው አካለ ክፍሉ ከአነስተኛ እቃዎች እስከ ቀላል መጠን ያላቸው ሸክሞችን በጀርባው መሸከም ያስችለዋል፤ እንዲሁም አስቸጋሪ በሆነ መሬት አቀማመጥ ላይ የረጋ እንቅስቃሴ ለማድረግ እግሮቹ ላይ ጎማዎች ይገጠሙለታል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0