ሱዳን የፀጥታው ምክር ቤት በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ላይ የመሳሪያ ማዕቀብ እንዲጥልና ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን በሽብርተኝነት እንዲፈርጅ ጥሪ አቀረበች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሱዳን የፀጥታው ምክር ቤት በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ላይ የመሳሪያ ማዕቀብ እንዲጥልና ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን በሽብርተኝነት እንዲፈርጅ ጥሪ አቀረበች
ሱዳን የፀጥታው ምክር ቤት በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ላይ የመሳሪያ ማዕቀብ እንዲጥልና ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን በሽብርተኝነት እንዲፈርጅ ጥሪ አቀረበች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 05.11.2025
ሰብስክራይብ

ሱዳን የፀጥታው ምክር ቤት በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ላይ የመሳሪያ ማዕቀብ እንዲጥልና ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን በሽብርተኝነት እንዲፈርጅ ጥሪ አቀረበች

በተመድ የሱዳን መልዕክተኛ ሀሰን ሀሚድ ሀሰን፤ አቡዳቢ በአማፂነት ለተፈረጀው የፈጥኖ ደራሽ ኃይል የጦር መሳሪያ እና ገንዘብ ድጋፍ እያደረገች ነው ሲሉ ከሰዋል፡፡

ይህን ድጋፍ ለማስቆም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ከፍተኛ ጫና እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡ የሱዳን ቀውስ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዝምታን ምርጫው በማድረጉ የተነሳ የመነጨ ነው ሲሉም አክለዋል፡፡

ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በአል-ፋሸር የሚገኘውን የሱዳን ጦር ዋና መምሪያ ከ18 ወራት ውጊያ በኋላ መቆጣጠሩን ጥቅምት 16 አስታውቋል፡፡ የሱዳን ጦር ዋና አዛዥ አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን ወታደሮቻቸው ከከተማዋ እንደወጡ ባሳለፍነው ማክሰኞ አረጋግጠዋል፡፡

የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰሜን ዳርፉር ዋና ከተማ የጅምላ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ዙሪያ የሚወጡ ሪፖርቶች እጅግ አሳሳቢ መሆናቸውን ገልጾ፤ ሞስኮ ለሰላማዊ መፍትሄ ድጋፍ እንደምታደርግ በድጋሚ አረጋግጧል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0