ከ3,500 በላይ ወጣቶች የሩሲያ 89 ክልሎችን ሰንደቅ ዓላማ ይዘው ሞስኮ ሰልፍ ወጡ

ሰብስክራይብ

ከ3,500 በላይ ወጣቶች የሩሲያ 89 ክልሎችን ሰንደቅ ዓላማ ይዘው ሞስኮ ሰልፍ ወጡ

በሰሜናዊ ሞስኮ የወጣቶች ደማቅ ሰልፍ ተደርጎ እንደነበር በስፍራው የተገኘው የስፑትኒክ ዘጋቢ ዘግቧል።

"አደባባዩን በርካታ ብሔር ብሔረሰቦች በወከሉ እና የባህል አልባሳት የለበሱ ወጣቶች ሞልተውታል። የየክልላችንን ባንዲራ በአንድ ሰልፍ ይዘን ነበር” ሲሉ የዩናይትድ ሩሲያ ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ ኃላፊ አንቶን ዴሚዶቭ ለስፔትኒክ ተናግረዋል።

በዝግጅቱ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሩሲያን ብሄራዊ መዝሙር በጋራ በመዘመር ተጠናቋል።

በዛሬው ዕለት በመላው ሩሲያ የተከበረው የብሔራዊ አንድነት ቀን በእ.ኤ.አ በ1612 ሞስኮ ከፖላንድ ወራሪዎች በሕዝብ በጎ ፈቃደኛ ሠራዊት ነፃ የወጣችበት ቀን ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0