በአሜሪካ የቀረበው ጋዛን 'የሚያረጋጋት ኃይል' ላይ የተመድ ሥልጣን ሊኖረው ይገባል ሲሉ የድርጅቱ ዋና ጸሐፊ ተናገሩ
19:12 04.11.2025 (የተሻሻለ: 19:14 04.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በአሜሪካ የቀረበው ጋዛን 'የሚያረጋጋት ኃይል' ላይ የተመድ ሥልጣን ሊኖረው ይገባል ሲሉ የድርጅቱ ዋና ጸሐፊ ተናገሩ
ከጦርነቱ በኋላ ያለው የሽግግር ጊዜ በጋዛ ሰርጥ ውስጥ ያለውን ሙሉ ሥልጣን ወደ ፍልስጤም አስተዳደር እንዲሸጋገር ማድረግ አለበት፤ ሲሉ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በዓለም አቀፍ የማኅበራዊ ልማት ጉባኤ ጎን ለጎን ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡
አሜሪካ ለበርካታ የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት አባላት በትንሹ ለሁለት ዓመታት በጋዛ ውስጥ የዓለም አቀፍ የደህንነት ኃይሎችን ለመፍጠር የሚያስችል ረቂቅ የውሳኔ ሐሳብ ልካለች፤ ሲል የአሜሪካ ኒውስ ፖርታል እጁ የገባውን የሰነድ ግልባጭ በመጥቀስ ቀደም ብሎ ዘግቧል።
የታቀደው ዓለም አቀፍ የደህንነት ኃይል ከኢንዶኔዢያ፣ አዘርባጃን፣ ግብፅ እና ቱርክ የሚውጣጣ ሲሆን ዶናልድ ትራምፕ በሊቀ-መንበርነት በሚመሩት "የሰላም ቦርድ" ስር እንደሚንቀሳቀስ ሕትመቱ አመልክቷል።
የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ድርድርን ተከትሎ ኃይሉ ጥር ወር ውስጥ እንዲሰማራ መታቀዱን ዘገባው አመልክቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X